አርጋኖን በግእዝ እና በአማርኛ | Arganon Android

አርጋኖን በግእዝ እና በአማርኛ | Arganon

ሙሉ መጽሐፈ አርጋኖን በግእዝ፣ በአማርኛ እና በድምጽ ንባብ | Arganon in Amharic & Ge'ez with Audio

Overview

Features & Capabilities

በአባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ የተደረሰው ታላቁን የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም የምስጋና መጽሐፍ «አርጋኖን»ን በግእዝ፣ በአማርኛ እና በድምጽ ንባብ በቀላሉ የያዘ መተግበሪያ

🔵የመተግበሪያው ልዩ ገጽታዎች (App Features)፦
• በየዕለቱ የተከፋፈለ፦ የሰባቱን ቀናት ጸሎት በቀላሉ ለመቀያየርና ለማንበብ በሚያመች መልኩ የተደራጀ።
• ቋንቋና ትርጉም፦ በግእዝና በአማርኛ ብቻውን ወይም ሁለቱንም ቋንቋዎች ጎን-ለጎን (Parallel) ለማንበብ የሚያስችል።
• የድምጽ ንባብ (Audio)፦ እያነበቡ በተመሳሳይ ሰዓት በድምጽ ለማዳመጥ የሚያስችል።
• ያለ በይነመረብ የሚሰራ (Offline)፦ አንዴ ዳውንሎድ ካደረጉት በኋላ ያለ ኢንተርኔት መስራት ይችላል
• ለአይን ምቹ፦ የጽሑፉን መጠን (Font size) ለማስተካከል፣ እንዲሁም የጀርባ ቀለሙን (Theme/Background) ለቀንና ለማታ ንባብ ምቹ አድርጎ ለመቀየር የሚያስችል።

📖 ስለ መጽሐፈ አርጋኖን፦
«አርጋኖን» የሚለው ቃል መነሻው የግሪክ ቋንቋ ሆኖ ትርጉሙም «ምስጋና» ማለት ሲሆን፤ በመዝሙረ ዳዊት ላይ ከሚገኘው ዐሥር አውታር ካለው የዳዊት የዜማ ዕቃ (በገና) ጋር አብሮ የሚተረጎም፣ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ታሪክ ውስጥ እጅግ የከበረና ጥልቅ ምስጢርን ያዘለ የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም የምስጋናና የጸሎት መጽሐፍ ነው።
«አርጋኖነ ውዳሴ»፣ «መሰንቆ መዝሙር» እና «ዕንዚራ ስብሐት» በሚሉ ስያሜዎችም የሚታወቀውን ይህንን ሰማያዊ መጽሐፍ የደረሱት በ፲፬ኛው መቶ ክፍለ ዘመን የነበሩት ታላቁ ኢትዮጵያዊ ሊቅ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ ሲሆኑ፤ ሊቁ በሐይቅ ደብረ ነጎድጓድ ገዳም በነበራቸው ቆይታ በጽኑ ጸሎትና በእንባ ፈጣሪያቸውን ሲማጸኑ እመቤታችን ከሊቀ መላእክት ቅዱስ ዑራኤል ጋር ተገልጻ የሕይወት ጽዋዕን ካጠጣቻቸውና የሰማይና የምድር ምስጢር ከተገለጠላቸው በኋላ በመንፈስ ቅዱስ ምሪት ያበረከቱት ድንቅ መጽሐፍ ነው።
ገድላቸው እንደሚያስረዳው የዚህን መጽሐፍ አጻጻፍ ታሪክ ልዩ የሚያደርገው፣ ሊቁ በቀን የጻፉት ቀለም በማግስቱ እየጠፋ ሲያስጨንቃቸው እመቤታችን በክብር ተገልጻ መጽሐፉ በእርሷ ዘንድ እንዳለና ከአርያም ኃይልን ተላብሰው እንዲጽፉት ፈቃዷን የሰጠችበት መሆኑ ነው። በዚህም መሠረት መጽሐፉ የእመቤታችንን ንጽሕና፣ ቅድስናና ወላዲተ አምላክነት ከተለያዩ የብሉይና የሐዲስ ኪዳን ምስጢራት ጋር እያመሰጠረ ከማብራራቱም ባሻገር፣ ስለ አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ የማዳን ሥራ፣ ሕማም፣ ስቅለትና መለኮታዊ ክብር አምልቶና አስፍቶ ይመሰክራል።
ይህ በቅዱሳን ዘንድ እጅግ የተወደደና በአጋንንት ዘንድ እንደ እሳት የሚፈራ የጸሎት መሣሪያ አዘውትረው ለሚጸልዩት መንፈሳዊ ዕውቀትን የሚያሰፋና የእግዚአብሔርን ጸጋ የሚያስገኝ ታላቅ የበረከት ምንጭ በመሆኑ፣ ምእመናን ይህንን ጥልቅ ታሪካዊ ጸሎት ባሉበት ቦታ ሆነው በማንኛውም ሰዓት በቀላሉ እንዲጠቀሙበት ይህ መተግበሪያ ተዘጋጅቷል።
━━━━━━━━━━━━━
Read and listen to 'Arganon'—the profound Ethiopian Orthodox book of praises dedicated to the Holy Virgin Mary, written by Abba Giorgis of Gasicha. Easily access the complete text in Ge'ez, Amharic, and full Audio right from your phone.

🔵 Key App Features:
• Organized by Days: Perfectly structured into 7 days of prayer with easy navigation and seamless switching.
• Bilingual & Parallel Reading: Read in Ge'ez, Amharic, or both side-by-side (parallel mode) for better understanding.
• Audio Integration: Listen to the spiritual audio while reading along simultaneously.
• Works Offline: It can work without an internet connection once downloaded.
• Reading Comfort: Fully adjustable font sizes and customizable themes/backgrounds (Day & Night modes) for a comfortable and strain-free reading experience.

📖 About The Book of Arganon:
"Arganon" originates from a Greek word meaning "Praise" and is associated with the ten-stringed harp of David. It is one of the most revered and spiritually profound prayer books of the Ethiopian Orthodox Tewahedo Church, dedicated to praising the Virgin Mary.
Written in the 14th century by the great Ethiopian scholar Abba Giorgis of Gasicha, this heavenly book was revealed through divine inspiration. While in deep prayer at the Hayq Estifanos Monastery, Abba Giorgis was visited by the Virgin Mary and Archangel Urael, who revealed the mysteries of heaven and earth to him.
The book profoundly explains the purity and holiness of the Virgin Mary, intertwining mysteries from both the Old and New Testaments. Furthermore, it deeply testifies to the saving work, crucifixion, and divine glory of our Lord Jesus Christ. Loved by saints and feared by evil spirits, Arganon is a powerful spiritual weapon and a vast source of blessings. This app is beautifully designed to help believers easily access and pray this historical and graceful prayer anywhere, anytime

User Growth & Download Statistics

App
By:
Nigat Systems
Downloads:
22,182 2.01K
Version:
1.0.2 Last updated: 2026-05-11
Version code:
3
Creation date:
2026-05-10
Publisher country:
ET ET
Permissions:
  • com.google.android.gms.permission.AD_ID Moderate risk
  • android.permission.ACCESS_ADSERVICES_AD_ID Low risk
  • android.permission.ACCESS_ADSERVICES_ATTRIBUTION Low risk
  • android.permission.ACCESS_ADSERVICES_TOPICS Low risk
  • android.permission.FOREGROUND_SERVICE Low risk
  • android.permission.FOREGROUND_SERVICE_MEDIA_PLAYBACK Low risk
  • android.permission.INTERNET Low risk
  • android.permission.POST_NOTIFICATIONS Low risk
  • android.permission.READ_APP_BADGE Low risk
  • android.permission.RECEIVE_BOOT_COMPLETED Low risk
  • See more
Size:
31.01MB
Email:
ni*****@gmail.com
URLs:
Website ,Privacy policy
Full description:
See detailed description
Source:
Google Play Store
Data ingested on:
2026-07-29
Compare stats and ranking:

Contact the developer

Chrome-Stats does not own this Android app. Please use these information below to contact the Android app developer.
Developed by:
Nigat Systems
Google Play Store
https://play.google.com/store/apps/details?id=com.nigatsystems.arganon
Email:
ni*****@gmail.com
Website:
https://nigatsystems.com

Best አርጋኖን በግእዝ እና በአማርኛ | Arganon Alternatives

Here are some Android apps that are similar to አርጋኖን በግእዝ እና በአማርኛ | Arganon: